Search

በክርስቲያን እምነት ላይ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤

ርዕስ 1፡ ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ መወለድ፤

1-4. በኢየሱስ ማመን አለብን? 

አዎ ማመን ይኖርብናል፡፡ ምክንያቱም እርሱ እጅግ ጻድቅ የሆነ ጌታችንና ይህም የእርሱ ፈቃድ ነውና፡፡ ‹‹መዳንም በሌላ በማንም የለም፡፡ እንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና፡፡›› (የሐዋርያት ሥራ 4፡12) ሌላ አዳኝ የለም፡፡ መዳንና ዳግም መወለድ የምንችለው በእርሱ በማመን ብቻ ነው፡፡ ሰማይ መግባትና ለዘላለም መኖር የምንችለው በእርሱ በማመን ብቻ ስለሆነ በእርሱ እምነት ሊኖረን ይገባል፡፡