Search

በክርስቲያን እምነት ላይ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤

ርዕስ 2፡ መንፈስ ቅዱስ፤

2-6. በልሳን መናገር ለዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ መኖር ማረጋገጫ አይደለምን? እንዲህ ካልሆነ መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን መኖሩን በምን እናውቃለን? 

በልሳን ስለተናገሩ ብቻ ዘለቄታዊውን መንፈስ ቅዱስ ለመቀበሉ ማረጋገጥ አንችልም፡፡ በአጋንንት የተያዙ ሰዎችም ሳይቀሩ በልሳን ይናገራሉ፡፡ አጋንንቶች ሰዎች በኢየሱስ ክርስቶስ ስም ስር ሆነው እንግዳ በሆኑ ልሳኖች እንዲናገሩ ማድረግ እንደሚችሉ ማወቅ ይገባናል፡፡ 
በልሳን መናገር ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ለመኖሩ ማስረጃ ነው የምንል ከሆነ ይህ በእርግጠኝነት ከመጽሐፍ ቅዱስ አቋም አንጻር የተሳሳተና እኛንም መንፈስ ቅዱስን በመሳደብ ሐጢያት ውስጥ ያስቀምጠናል፡፡ 1ኛ ቆሮንቶስ 12፡30 እንዲህ ይላል፡- ‹‹ሁሉስ የመፈወስ ስጦታ አላቸውን? ሁሉስ በልሳኖች ይናገራሉን? ሁሉስ ይተረጉማሉን?›› መንፈስ ቅዱስ የእግዚአብሄር መንፈስ ስለሆነ በምንም መንገድ ከሐጢያት ጋር አብሮ አይሆንም፤ በልቡ ውስጥ ሐጢያት ባለበት ግለሰብ ውስጥም ሊያድር አይችልም፡፡ 
አንድ ሰው በልሳን ስለተናገረ ብቻ መንፈስ ቅዱስን መቀበሉን ማመን አይገባንም፡፡ ነገር ግን በመጀመሪያ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል በማመን የሐጢያት ይቅርታ መቀበሉን መመርመር ይገባናል፡፡ ልሳንን እንደ መተርጎም ያለ አንዳች አይነት ልዩ ልምምድ ስላለው ብቻ መንፈስ ቅዱስን እንደተቀበለ የሚያስብ ሰው ካለ ሸር በተሞላበት የሰይጣን ማታለያ እየተጭበረበረ ሊሆን ይችላል፡፡ (2ኛ ተሰሎንቄ 2፡10) መንፈስ ቅዱስ በቃሎቹ አማካይነት የሐጢያት ይቅርታን ለተቀበሉ ሰዎች በእግዚአብሄር የተሰጠ ስጦታ ነው፡፡ 
ለሁለተኛው ጥያቄ መልስ ይሆን ዘንድ መንፈስ ቅዱስ ራሱ አምላክና የእውነት መንፈስ ነው፡፡ ስለዚህ ከውሃውና ከመንፈሱ ወንጌል ጋር አብሮ ይሰራል፡፡ እርሱ በሰው ፈቃድ መሰረት አይሰራም፡፡ እርሱ ሐጢያተኞች የውሃውንና የመንፈሱን ወንጌል እንዲያምኑ ይመራል፤ ለጻድቃን እውነቱን ያስተምራል፤ የእግዚአብሄር ፈቃድ የሆነውንም ወንጌል ከእነርሱ ጋር አብሮ በጸጥታ ይሰብካል፡፡ እርሱ እሳት መሰል በሆኑ ስሜቶች ወይም መቋቋም በማይቻሉ የሰውነት እንቅጥቃጤዎች በኩል አይመጣም፡፡ እግዚአብሄር እውነተኛውን የውሃና የመንፈስ ወንጌል በመታዘዝ ሐጢያቶቻቸው ለተደመሰሱላቸው ጻድቃን መንፈስ ቅዱስን ሰጠ፡፡ እነርሱ የእግዚአብሄር ልጆች መሆናቸውንም አስተማራቸው፡፡ መንፈስ ቅዱስ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል አማካይነት ሐጢያት አልባና ሙሉ በሙሉ ጻድቅ እንደሆኑ በጻድቃን ልቦች ውስጥ ይመሰክራል፡፡ 
ስለዚህ አንድ ሰው በልሳን ቢናገር ነገር ግን አሁንም በልቡ ውስጥ ሐጢያት ካለበት በውስጡ ያለው መንፈስ በእርግጠኝነት መንፈስ ቅዱስ ሳይሆን የሰይጣን መንፈስ ነው፡፡ በልባችሁ ውስጥ ዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ እንዲኖር የምትፈልግ ከሆነ በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል ማመን ይኖርብሃል፡፡ ያን ጊዜ ጌታ በዘለቄታዊው መንፈስ ቅዱስ ይባርክሃል፡፡