Search

በክርስቲያን እምነት ላይ አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤

ርዕስ 4፡ መጽሐፎቻችን ከሚያነቡ አንባቢዎች አዘውትረው የሚጠየቁ ጥያቄዎች፤

4-6. ከአስተምህሮቶችህ የኢየሱስ ጥምቀት ለደህነናችን አፈላጊ እንደሆነ አውቃለሁ፡፡ ታዲያ የአማኞች የውሃ ጥምቀትን በሚመለከትስ ይህም ደግሞ ለእያንዳንዱ ቅዱስ ግዴታ ነውን ከዚህ በተጨማሪም በአካባቢዩ እኔን ሊያጠምቀኝ የሚችል ማነም ዳገመኛ የተወለደ አገልጋይ የለም፡፡

ድረ ገጻችንን እንዳነበብከው የአማኞች የውሃ ጥምቀት በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል የሚያምኑ አማኞች በአካል የሚናዘዙት ኑዛዜ ነው፡፡ በሌላ አነጋገር በዚህ የጥምቀት ስርዓት ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ በጥምቀቱና በስቅለቱ ባጠናቀቀው ፍጹም ደህንነት ላይ ያላቸውን እምነት መመስከር ይችላሉ፡፡ 
   
ሐጢያተኝነታችንን ስንናዘዝ፣ ለሲዖል የተመደበውን ዕጣ ፈንታችንን አውቀን ስንቀበልና በውሃውና በመንፈሱ ወንጌል እምነት ሲኖረን ሁላችንም ዳግመኛ መወለድ እንችላለን፡፡ እንደዚያ ነው፡፡
ታዲያ የውሃ ጥምቀት ለአማኙ ምንድነው? ከእንግዲህ ወዲያ ዋጋ የለውም? በእርግጥ ለደህንነታችን አስፈላጊ ሁኔታ አይደለም፤ ነገር ግን ይህ የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ትዕዛዝ ነው፡፡ (ማቴዎስ 28፡19) 
  
የምትችል እስከሆነ ድረስ ጥምቀትን ብትቀበል የተሻለ ነው፡፡ ነገር ግን እንደነገርከኝ ከውሃና ከመንፈስ ዳግመኛ ከተወለደ ሰው ጋር መገናኘት ያስፈልግሃል፡፡ አንተ ከምታውቃቸው ሰዎች መካከል ዳግመኛ የተወለደ ቅዱስ ካለ እንዲያጠምቅህ ልትጠይቀው ትችላለህ፡፡ ከስርዓቱ በፊት በኢየሱስ ጥምቀትና በመሰቀል ላይ ሞቱ ያለህን እምነት መመስከር ይኖርብሃል፡፡ ከዚያም ግለሰቡ እጆቹን በራስህ ላይ በመጫን ከታች ያለውን አረፍተ ነገር ማወጅ ይኖርበታል፡-   
‹‹በእግዚአብሄር አብ፣ ወልድ በሆነው ኢየሱስ ክርስቶስና በመንፈስ ቅዱስ ስም አንተን ወንድም ኮሊንን አጠምቅሃለሁ፡፡›› መጽሐፍ ቅዱሳዊ ጥምቀት በሙሉ ጥልመት መደረግ ይኖርበታል፡፡
ባልና ሚስት በሠርግ ስርዓት አማካይነት ሕጋዊ ጥንዶች መሆናቸውን እንደምናውቅ ሁሉ የአማኞች ጥምቀትም የታመነ ነው፡፡ ስለዚህ የቅዱሳኖች የጥምቀት ስርዓት እንዲህ ላለው ውስጣዊ አመኔታ ውጫዊ እወጃ ነው፡፡ በእግዚአብሄር፣ በቅዱሳኖችና በአለም ፊት በጥምቀቱና በመስቀሉ ላይ ያለንን አመኔታ በውሃ ጥምቀት አማካይነት ስናውጅ እምነታችን ይበልጥ የማይበገር ይሆናል፡፡
ሆኖም አብርሃም የመገረዝን ምልክት የረቀበለው ገና ሳይገረዝ በእምነት ጻድቅ መሆኑ ከመረጋገጡ ከረጅም ጊዜ በኋላ እንደነበር መርሳት አይገባህም፡፡ (ሮሜ 4፡11) በሌላ አነጋገር እግዚአብሄር በቃሉ ላይ ባለው እምነቱ ቀድሞውኑም ለደረሰበት ደህንነት ምልክት እንዲሆን ግርዘትን ሰጠው፡፡ 
ልክ እንደዚሁ የውሃ ጥምቀትም በጥምቀቱና በስቅለቱ ላይ ባላቸው እምነት አማካይነት የሐጢያቶቻቸውን ስርየት ለተቀበሉ ዳግመኛ የተወለዱ ሰዎች ውጫዊ ስርዓት ነው፡፡