ቁስ፡ ከነሐስ የተሠራና ሁሌም በውሃ የተሞላ፡፡
መንፈሳዊ ትርጉም፡ ነሐስ ማለት የሰው ዘር ሐጢያቶች በሙሉ ፍርድ ማለት ነው፡፡ ኢየሱስ የሰውን ዘር ሐጢያቶች ኩነኔ በሙሉ ለመሸከም በዮሐንስ በመጠመቅ የዓለምን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ ወሰደ፡፡ ስለዚህ የመታጠቢያው ሰን ትርጉም እነዚህ ሐጢያቶቻችን በሙሉ በጥምቀቱ ወደ ኢየሱስ መሻገራቸውን በማመን ከሐጢያቶቻችን በሙሉ መታጠብ የምንችል መሆናችንን የሚያሳይ ነው፡፡
በመገናኛው ድንኳን ውስጥ የሚያገለግሉት ካህናቶችም እንደዚሁ እንዳይሞቱ ወደ መገናኛው ድንኳን ከመግባታቸው በፊት እጆቻቸውንና እግሮቻቸውን ይታጠባሉ፡፡ ነሐስ በሐጢያቶች ላይ የሚመጣውን ፍርድ ያመለክታል፡፡ በመታጠቢያው ሰን ውስጥ ያለው ውሃም ኢየሱስ የዓለምን ሐጢያቶች በራሱ ላይ የወሰደበትን ከዮሐንስ የተቀበለውን ጥምቀት ያመለክታል፡፡ በሌላ አነጋገር የመታጠቢያው ሰን ኢየሱስ ወደ እርሱ የተሻገሩትን ሐጢያቶች በሙሉ በራሱ ላይ መውሰዱንና የእነዚህን ሐጢያቶች ኩነኔ መሸከሙን ይነግረናል፡፡ በብሉይ ኪዳን የመታጠቢያው ሰን ማለት የመገናኛው ድንኳን ሰማያዊ ማግ ሲሆን በአዲስ ኪዳን ደግሞ ኢየሱስ ከዮሐንስ የተቀበለው ጥምቀት ማለት ነው፡፡ (ማቴዎስ 3፡15፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡21)
ስለዚህ የመታጠቢያው ሰን የኢየሱስን ጥምቀት ያመለክታል፡፡ ይህም ኢየሱስ ሐጢያቶቻችንን፤ በየቀኑ የምንሰራቸውን ሐጢያቶቻችንን ጨምሮ የመሸከሙንና ከ2,000 ዓመታት በፊት ከአጥማቂው ዮሐንስ በተቀበለው ጥምቀቱ አማካይነት ሁሉንም በአንድ ጊዜ ያስወገደ በመሆኑ እውነት እምነታችንን የምናጸናበት ስፍራ ነው፡፡