የመጀመሪያው መደረቢያ የተሰራው ከሰማያዊ፣ ከሐምራዊ፣ ከቀይ ማግና ከጥሩው በፍታ ተፈትለው ከተሰሩና ውብ የሆኑ የኪሩቤል ንድፎች ከተጠለፈባቸው መጋረጆች ነበር፡፡ ይህ የሚገልጠው መሲሁ በሰማያዊ፣ በሐምራዊ፣ በቀይ ማግና በጥሩ በፍታ በኩል እንደሚመጣና በእርሱ የሚያምኑትን ሁሉ ከሐጢያቶቻቸውና ከኩነኔ እንደሚያድናቸው ነው፡፡
የመገናኛው ድንኳን ሁለተኛው መደረቢያ የተሰራው ከፍየል ጠጉር ነበር፡፡ ይህም የሚመጣው መሲህ የሰውን ዘር ከሐጢያቶቻቸውና ከእነዚህ ሐጢያቶቻቸው ኩነኔ በመታደግ እንደሚያጸድቃቸው ይነግረናል፡፡
የመገናኛው ድንኳን ሦስተኛው መደረቢያ ከቀይ አውራ በግ ቁርበት የተሰራ ነበር፡፡ ይህም መሲሁ ወደዚህ ምድር እንደሚመጣ፣ በመጠመቀም የዓለምን ሐጢያቶች እንደሚወስድ፣ እንደሚሰቀልና በዚህም ለሕዝቡ ሐጢያቶች የመስዋዕት ቁርባን እንደሚሆን ያሳያል፡፡
አራተኛው የመገናኛው ድንኳን መደረቢያ ከአቆስጣ ቁርበት የተሰራ ነበር፡፡ የአቆስጣው ቁርበት እኛን ከዓለም ሐጢያቶች ለማዳን ሲል ወደ ሰብዓዊ ፍጡራን ደረጃ ራሱን ዝቅ ያደረገውን የኢየሱስ ክርስቶስን ስዕል ያሳየናል፡፡