ቅድስተ ቅዱሳኑ እግዚአብሄር የሚያድርበት ስፍራ ነው፡፡ በቅድሰተ ቅዱሳኑ ውስጥ ክንፎቻቸውን የዘረጉ ሁለት ኪሩቤሎች ከላይ ሆነው የምስክሩን ታቦት የሸፈነውን ክዳን ተመለከቱ፡፡ በሁለቱ ኪሩቤሎች መካከል ያለ ባዶ ስፍራ የምህረት መቀመጫ ተብሎ ይጠራል፡፡ የምህረት መቀመጫው እግዚአብሄር ጸጋውን ለእኛ የለገሰበት ነው፡፡ የምስክሩ ታቦት መሸፈኛ ሊቀ ካህኑ ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠውን የመሰዋዕቱን ደም በምህረት መቀመጫው ላይ ሰባት ጊዜ ስለረጨው በደም ተበክሎ ነበር፡፡
ለእስራኤላውያን ሐጢያቶች ስርየት ለመስዋዕት የቀረበውን ፍየል ደም ይዞ በዓመት አንድ ጊዜ ወደ ቅድስተ ቅዱሳን መግባት የሚችለው ሊቀ ካህኑ ብቻ ነው፡፡ ይህንን ያደረገው የመገናኛው ድንኳን ቅድስተ ቅዱሳን የሆነው የእግዚአብሄር ቤት የሐጢያተኞችን ሐጢያቶች ለመደምሰስ እጆቹን በራሱ ላይ ጭኖ የመስዋዕቱን ደም ካልያዘ በስተቀር ሊገባበት የማይችልበት ቅዱስ ስፍራ ነበርና፡፡
እግዚአብሄር እንዲህ በምህረት መቀመጫው ላይ ወረደና ምህረቱን ለእስራኤል ሕዝብ ለገሰ፡፡ በዚህ ለሚያምኑ ሰዎች የእግዚአብሄር በረከቶች፣ ጥበቃና ምሪት ይጀምራል፡፡ ከዚያ ጀምሮ እነርሱ የእግዚአብሄር እውነተኛ ሕዝብ ይሆኑና ወደ ቅድስቱ ስፍራ ለመግባት ብቁ ይሆናሉ፡፡